አዋሽ መልካሳ ኬሚካዊ ፋብሪካ (አመኬፋ)
ፋብሪካው በምስራቅ ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ 105 ኪሜ እና ከአዳማ /ናዝሬት/ ወደ አሰላ በሚወስደው መንገድ 15 ኪ.ሜ. ላይ በአዋሽ መልካሳ ይገኛል።
ፋብሪካው በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አቦ ሳሪስ አካባቢ የሽያጭ ማእከል እና መደብር አለው፡፡
አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ; በዘመናዊ የማምረት ቴክኖሎጂ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የማምረት ልምዶች፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የኬሚካል ምርቶችን በማምረት፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ጥሬ ዕቃዎችን በመጠቀም፣ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ምንጮች. ፋብሪካው የአገር ውስጥ ገበያን እየሸፈነ በመሆኑ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው። ፋብሪካው የተለያዩ ጥራት ያላቸውን የኬሚካል ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ለሀገር ልማትና ለኢንዱስትሪ ዕድገት የላቀ ሚና ይጫወታል። ምርቶቹን ለአንዳንድ ጎረቤት ሀገራት በማቅረብም የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገሪቱ ያመጣል።
በፋብሪካችን የምናመርታቸው ምርቶች
MAJOR USERS OF SULPHURIC ACID:
- አሉሚኒየም ሰልፌት ለማምረት
- ለወረቀት እና የፓምፕ ፋብሪካ
- ለስኳር ኢንዱስትሪ
- ለቆዳ ፋብሪካዎች
- ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች
- ለመጠጥ ኢንዱስትሪዎች
- ለሳሙና ኢንዱስትሪዎች
- ለመኪና ባትሪዎች
- Steel manufacturing /Metallurgy
- ለጥጥ ዘር ዝግጅት
- ለኮላ ማምረቻ
- ለማዳበሪያ ኢንዱስትሪዎች
- ለአትክልት እርሻዎች; እንደ አበባ, አትክልት እና ፍራፍሬ.
MAJOR USERS OF HYDROGEN PEROXIDE:
- ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ
- ለቆዳ ኢንዱስትሪ
- ለማዕድን እና ብረት ማምረት
- ለኤሌክትሮኒክስ ኢንዱስትሪ
- ለኦርጋኒክ ኬሚካል ኢንዱስትሪዎች
- ለአረፋ እና የጎማ ኢንዱስትሪዎች
- ለኬሚካል ኢንዱስትሪ
- ለፋርማሲዩቲካል እና ኮስሜቲክስ ኢንዱስትሪ
- ለምግብ ማሸጊያ ኢንዱስትሪዎች እና ወዘተ
የአሉሚኒየም ሰልፌት ዋና ዋና ጥቅሞች፡-
- ለመጠጥ ውሃ ማጣሪያ
- ቆሻሻ ውሃ ለማጽዳት
- ለፐልፕ እና ለወረቀት ኢንዱስትሪዎች
- ለቆዳ / የቆዳ ፋብሪካ / ኢንዱስትሪዎች
- ለምግብና መጠጥ
- ለስኳር ኢንዱስትሪ
የእኛ የቅርብ ጊዜ ዜናዎች
በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ የሙያ ደህንነት፣ ጤንነትና አከባቢ ጥበቃ መምሪያ ለፋብሪካው ሰራተኞች ከሰኔ 17- 20/2016 ዓ.ም በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።የስልጠናው ዋና ዓላማም በፋብሪካ ውስጥ(በስራ ቦታ) ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ፈጣን ምላሽ በመስጠት በሰውና በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችልን አደጋ መታደግ ለማስቻል ነው።የሥራ ቦታ ደህንነት (Workplace Safety) ፣ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት እና ምላሽ እቅድ (Emergency Preparedness and Response Plan) እና የእሳት አደጋ መከላከል(Fire Prevention) በስልጠናው የተካተተቱ ዋና ዋና ርእሰ ጉዳዮች ናቸው።አደጋን አስቀድሞ በመከላከልና በድንገት አደጋ ቢያጋጥም መወሰድ ሰለሚገባቸው እርምጃዎች ግንዛቤ እንዳገኙ አንዳንድ ያነጋገርናቸው በስልጠናው ላይ የተሳተፉ የፋብሪካው ሰራተኞች ገልጸዋል።በተለይ ስልጠናው በተግባር የደገፈ መሆኑ የማይረሳና ሁላችንም ልንጠቀምበት የምንችል እንደሆነ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአዋሽ መልከሳ ኬሚካል ፋብሪካ በመገኘት ከኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮሮፖሬሽን ም/ዋ/ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ለማ ደንደና እና የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን ጉብኝት አድርገዋል፡፡ የሰልፈሪክ አሲድና የአሉሚኒየም ሰልፌት ፋብሪካዎች የመልሶ ማደስ(Rehabilitation) ያስፈለገበትን ምክንያት ፋብሪካዎቹን በአካል በማየትና በቀረበላቸው ገለፃ በመረዳት ለፕሮጀክቱ መሳካት የበኩላቸውን እገዛ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡